እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን።
ጻድቃን ሆይ፥ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ለቅኖች ምስጋና ይገባል። እግዚአብሔርን በመሰንቆ አመስግኑት፥ አሥር አውታርም ባለው በበገና ዘምሩለት። አዲስ ቅኔም ተቀኙለት፥ በእልልታም መልካም ዝማሬ ዘምሩ፤ የዳዊት መዝሙር። 33:1-3 ሃሌ ሉያ። እግዚአብሔርን በመቅደሱ አመስግኑት፤ በኃይሉ ጠፈር አመስግኑት።በችሎቱ አመስግኑት፤ በታላቅነቱ ብዛት አመስግኑት።በመለከት ድምፅ አመስግኑት፤ በበገናና በመሰንቆ አመስግኑት።በከበሮና በዘፈን አመስግኑት፤ በአውታርና በእምቢልታ አመስግኑት። ድምፁ መልካም በሆነ ጸናጽል አመስግኑት፤ እልልታ ባለው ጸናጽል አመስግኑት እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን። ሃሌ ሉያ።።የዳዊት መዝሙር150:1-6
No comments:
Post a Comment
Thanks for Visiting "Abebaw blogspot"